@MNG · 2025.04.20
ኤም ኤን ጂ የፊልም ኩባንያ እና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ለ100 አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ማዕድ የማጋራት ሥነ-ስርዓት አደረገ። #fikreselam በማዕድ ማጋራት ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሰላማዊት አየለ መንግስት ዜጎችን ለማገዝ እያደረገ ያለውን ጥረት አንስተው ይህ ማዕድን የማጋራት ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል። ኃላፊዋ አክለውም ልክ እንደ ኤም ኤን ጂ ሁሉ ሌሎች ተቋማትም ይህንን አርዓያነት በመከተል መሰል ተግባራትን ሊያከናውኑ እንደሚገባም አስታውሰዋል። ኩባንያው በቻለው መጠን ሁሉም ማህበረሰብ በዓልን በደስታ እንዲያሳልፍ ለማድረግ እየሞከረ እንደሚገኝ ያነሱት የኤም ኤን ጂ ም/ል ሥራ አስኪያጅ ማስተዋል ገድሉ፤ ኩባንያው ይህንን ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ቃል ገብተዋል። ኤም ኤን ጂ ፊልም እና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ከዚህ ቀደም በወደቁትን አንሱ የነድያን መርጃ ማሕበር እና በንህምያ የኦቲዝም ሴንተር በመገኘት መሰል ድጋፎችን ሲያደርግ እንደነበር በማዕድ ማጋራት መድረኩላይ ተነስቷል። https://www.facebook.com/story.php?story_fbid=1189460885907478&id=100045307342909&rdid=XMQT8nO65pMjbRee#
play