@MNG · 2025.04.22
ኤም ኤን ጂ የፊልም እና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ለ100 አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ማዕድ የማጋራት ሥነ-ስርዓት አደረገ። በማዕድ ማጋራት ሥነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሰላማዊት አየለ መንግስት ዜጎችን ለማገዝ እያደረገ ያለውን ጥረት አንስተው ይህ ማዕድን የማጋራት ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ኃላፊዋ አክለውም ልክ እንደ ኤም ኤን ጂ ሁሉ ሌሎች ተቋማትም ይህንን አርዓያነት በመከተል መሰል ተግባራትን ሊያከናውኑ እንደሚገባም አስታውሰዋል። ኩባንያው በቻለው መጠን ሁሉም ማህበረሰብ በዓልን በደስታ እንዲያሳልፍ ለማድረግ እየሞከረ እንደሚገኝ ያነሱት የኤም ኤን ጂ ም/ል ሥራ አስኪያጅ ማስተዋል ገድሉ፤ ኩባንያው ይህንን ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ቃል ገብተዋል። ኤም ኤን ጂ ፊልም እና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ከዚህ ቀደም በወደቁትን አንሱ የነድያን መርጃ ማሕበር እና በንህምያ የኦቲዝም ሴንተር በመገኘት መሰል ድጋፎችን ሲያደርግ እንደነበር በማዕድ ማጋራት መድረኩላይ ተነግሯል። Arts tv ሊንክ! 1.https://www.facebook.com/100064752820499/posts/pfbid0c2kEiV2pFFqnoF6jEJng3M7tY3gNyfbSJWVaRrvDsdQfMmdyQ29rUpnzB9jMwjn9l/?app=fbl 2.https://t.me/Arts_tv/15379?single 3.https://t.me/ArtsTvWorldTelegram/1618?single
play